የአማራ ክልል መንግሥት ለጎንደር ከተማ የ100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

13

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል መንግሥት ለጎንደር ከተማ የ100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ለጎንደር፣ ለባሕር ዳር እና ለደሴ ከተሞች የኮሪደር ልማት ሥራዎች ለእያንዳንዳቸው 100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

” ኑ ጎንደርን እንሞሽር” የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር እንደቀጠለ ነው።

በመርሐ ግብሩ ላይ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የሶማሌ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጦፋ ሙሐመድ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ ሚኒስትሮች፣ የክልል እና የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ መሪዎች፣ ባለሀብቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“ጎንደር የኢትዮጵያውያን የጋራ የእጅ ሥራ ውጤት ናት” ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
Next article“አባቶቻችን የሠሩትን ቅርስ ማደስ ብቻ ሳይኾን የዕድገት ሕልማቸውንም ዕውን ለማድረግ እየሠራን ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ