
ባሕር ዳር: ሚያዚያ: 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረክሂ ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል። ውይይቱ የሁለቱን ሀገራት የባሕል፣ የኪነ ጥበብ እና ስፖርት ዘርፍ ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጓል።
በውይይቱ ኢትዮጵያ ካላት የብዝኅ ባሕል ባለቤት እና ታሪክ አንጻር ከሩሲያ ጋር በዘርፎቹ በጋራ መስራቷ ያለው አስፈላጊነት ተነስቷል።
ኢትዮጵያ ለብሪክስ አባል ሀገራት ባሕል እና የኪነ ጥበብ ሃብቷን ለማስተዋወቅ እንዲሁም የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን ለማጠናከር እያከናወነች ያለውን ሥራ የሩሲያ መንግሥት በመደገፍ በትብብር እንደሚሠራም ተገልጿል።
ሁለቱ ወገኖች በቀጣይ የጋራ የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም የሀገራቱን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር መስማማታቸውን የባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
