
ወልድያ: ሚያዝያ 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የክልል እና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በራያ ቆቦ ወረዳ እና በቆቦ ከተማ አሥተዳደር በምርት እና በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ ፋብሪካዎችን ጎብኝተዋል።
“ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት” በሚል መሪ መልዕክት የሰሜን ወሎ ዞን ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ያዘጋጀው ዞናዊ የማጠቃለያ ኘሮግራም በቆቦ ከተማ እየተካሄደ ነው።
የማጠቃለያ ኘሮግራሙ አንድ አካል የኾነው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ጉብኝት ተደርጓል።
የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እንድሪስ አብዱ እና ሌሎች የክልል እና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት በራያ ቆቦ ወረዳ እና በቆቦ ከተማ አሥተዳደር በምርት እና በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ ፋብሪካዎች ተጎብኝተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
