“ስኬታማ ተግባራትን ማስቀጠል፣ ታቅደው ያልተከናወኑትን ደግሞ በትጋት መከወን በቀሪ ወራት ይጠበቃል” ከንቲባ አዳነች አቤቤ

12

አዲስ አበባ :ሚያዝያ 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ከወረዳ እስ ከተማ አሥተዳደር ያሉ የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት እየተካሄደ ነው። በመድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደ ከተማ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውጤታማ ተግባራት ስለመከወናቸውን ገልጸዋል።

በመኾኑም ለውጤታማነት ምክንያት የኾኑ ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል ከሁሉም ፈጻሚ አካላት ይጠበቃል ብለዋል። “ስኬታማ ተግባራትን ማስቀጠል፣ ታቅደው ያልተከናወኑትን ደግሞ በትጋት መከወን በቀሪ ወራት ይጠበቃል”

የአሠራር ጉድለቶች እና የመልካም አሥተዳደር ችግሮች አሁንም ሕዝብን እያማረሩ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች ጉድለቶችን በማረም ቅሬታን መቀነስ እና ችግር የሚፈጥሩ መሪዎች ላይም ተጠያቂነትን ማስፈን ይገባል ብለዋል።

በቀጣይ ቀሪ ሦስት ወራት ፈጻሚ አካላት ከማኅበረሰቡ ጋር በመተባበር ለውጤት የሚያበቁ ተግባራትን በመከዎን የበጀት ዓመቱን በስኬት ለማጠናቀቅ መትጋት ይጠበቃል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ይኾናል።

ዘጋቢ፦ አዲሱ ዳዊት

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“መንግሥት በፈጠራ እና ክህሎት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Next articleከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በራያ ቆቦ ወረዳ እና በቆቦ ከተማ አሥተዳደር የሚገኙ የኢንቨስትመንት ሥራዎችን ጎበኙ።