“በክልሉ የተሟላ ሰላም ለማምጣት እየተሠራ ያለው ሥራ ውጤት እያመጣ ነው” አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር)

35

ደብረ ብርሃን: ሚያዝያ 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት በሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረ ማርያም ከሰም ወረዳ ኮረማሽ ንዑስ ወረዳ ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር ውይይት ተደርጓል። በውይይቱ የሰላም እና የልማት ጥያቄዎች በዘላቂነት እንዲፈቱ በተሳታፊዎች ተነስተዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ መካሻ ዓለማየሁ ከአንድ ዓመት በላይ ያስቆጠረው የሰላም ችግር ማኅበረሰቡን ከልማት ሥራው አስተጓጉሎት እንደቆየ አንስተዋል። በተደረገ ተከታታይ የሰላም ውይይት ችግሮች እየተቃለሉ ሕዝቡም ወደ ልማቱ እየተመለሰ መኾኑን ገልጸዋል።

በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አሥተባባሪ እና የከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን መሐመድ(ዶ.ር) የክልል ከፍተኛ መሪዎች እስከ ቀበሌ ድረስ ወርደው በማወያየት ሰላምን ለማጽናት የሠሩት ሥራ ውጤቱ በተግባር እየታየ ነው ብለዋል።

የተሟላ ሰላም ለማምጣት እየተሠራ ያለው ሥራ ውጤት እያመጣ መኾኑንም አንስተዋል። ማኅበረሰቡም የሚያነሳውን የልማት ጥያቄ ለመመለስ ሰላምን ማጽናት ቀዳሚው ተግባር እንደኾነም ገልጸዋል። ለዚህ ደግሞ ማኅበረሰቡ በባለቤትነት ሊያግዝ ይገባል ነው ያሉት።

በውይይቱ ላይ የሰሜን ሸዋ ዞን እና በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ አዋሳኝ የወረዳ መሪዎቸም ተገኝተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“በሙስና የተገኘ ገንዘብን የመሰወር እና ሽብርተኝነትን ለመደገፍ የሚደረጉ ጥረቶችን መከላከል ይገባል” የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ
Next articleየደሴ ከተማ አሥተዳደር በዝቅተኛ እና መካከለኛ ኑሮ ለሚገኙ ኑዋሪዎች የጋራ መኖሪያ ቤት ሊገነባ ነው።