
ባሕር ዳር:ሚያዝያ 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በግሪክ ፓርላማ አባልና የኦርቶዶክስ ኢንተርፓርሊያመንት ጉባኤ ኀላፊ ማክስሞስ ቻራኮፖሎስ (ዶ.ር) የተመራ የልኡካን ቡድን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ጉብኝት አድርጓል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ
ሁለቱ ሀገራት ለበርካታ ዓመታት ያዳበሩት ጠንካራ የመንግሥታት እና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከግሪክ ንግድና ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ልምድ መቅሰም እንደምትፈልግ እና ያላትን መልካም ተሞክሮም ለማካፈል ያላትን ዝግጁነት አንስተዋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ፣ የምዕራብ አውሮፓ ሀገራት እና የአውሮፓ ኅብረት የወዳጅነት ኮሚቴ ሰብሳቢ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ኢትዮጵያ እና ግሪክ ለረጅም ዓመታት ያላቸውን ወዳጅነት ወደላቀ ደረጃ ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
ሁለቱ ሀገራት በቴክኖሎጂ፣ በንግድ፣ በግብርና፣ በቱሪዝም፣ በኀይል እና በተለያዩ ዘርፎች ተባብረው ቢሠሩ ውጤታማ እንደሚሆኑ አመላክተዋል። የሁለቱ ሀገራት ምክር ቤቶች ተቀራርበው በመሥራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን ማጠናከር እንደሚገባቸውም ተናግረዋል፡፡ በግሪክ ፓርላማ አባልና የኦርቶዶክስ ኢንተርፓርሊያመንት ጉባኤ ኀላፊ ማክስሞስ ቻራኮፖሎስ (ዶ.ር) ግሪክ የአውሮፓ ኅብረት አባል እንደመሆኗ ኢትዮጵያን ከአውሮፓ ኅብረት ጋር ለማቀራረብ እንደምትሠራ ገልጸዋል፡፡
በቱሪዝም እና በግብርናው ዘርፍ ግሪክ ከኢትዮጵያ በርካታ ልምዶችን መቅሰም ስለምትፈልግ በዘርፉ አብሮ ለመሥራት ፍላጎት አለን ነው ያሉት። ግሪክ በኮንስትራክሽን፣ በባሕር ትራንስፖርት እና በተለያዩ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ያላትን ልምድ ለኢትዮጵያ ማካፈል እንደምትፈልግም ገልጸዋል።
ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የግሪክ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ያላቸውን ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ አንስተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን