የፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የዐይን ሞራ ግርዶሽ ሕክምና ለሚፈልጉ ሰዎች ጥሪ አቀረበ።

24

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ከግንቦት አጋማሽ ጀምሮ ነጻ የዐይን ሞራ ግርዶሽ ሕክምና እንደሚሰጥ የፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታውቋል።

የዐይን ሞራ ግርዶሽ በኢትዮጵያም ኾነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በመጀመሪያ ደረጃ የዐይን ሥውርነት የሚያስከትል በሽታ ነው። የቀዶ ጥገና ሕክምና ደግሞ ዋናው መፍትሔ ነው።

ችግሩን ለመቅረፍ የፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ”ኤች ሲ ፒ ኪዩር ብላይንድነስ” ጋር በመተባበር ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ከ20 ጊዜ በላይ የዐይን ሕክምና ሰጥቷል። በዚህም ከ12 ሺህ 500 በላይ ሰዎች አገልግሎቱን ማግኘታቸውን የሆስፒታሉ የዐይን ሕክምና ክፍል አሥተባባሪ ድረስ አለማየሁ ገልጸዋል።

ከግንቦት 15 እስከ 19/2017 ዓ.ም ባሉት ቀናት በፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነጻ የዐይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና እንደሚሰጥ ነው የተገለጹት።

በመኾኑም:-
👉 ከሚያዝያ 25 እስከ 26/2017 ዓ.ም ድረስ በመራዊ እና በዳንግላ ጤና ጣቢያዎች

👉 ከግንቦት 02 እስከ 03/2017 ዓ.ም ድረስ በሊበን እና በዱርቤቴ ጤና ጣቢያዎች

👉 ከግንቦት 09 እስከ 10/2017 ዓ.ም ድረስ በአዴት እና በወረታ ጤና ጣቢያዎች

👉 ከሚያዚያ 25 እስከ ግንቦት 10/2017 ዓ.ም ድረስ ደግሞ በፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የልየታ ሥራ የሚሠራ በመኾኑ ችግሩ ያለባቸው ሰዎች ቀርበው እንዲመዘገቡ አሥተባባሪው ጥሪ አቅርበዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየፈተና ውጤት ማሳወቅ
Next articleየደም ካንሰር እና ሕክምናው!