
ባሕር ዳር:ሚያዝያ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ደረጃ (6ኛ ክፍል) እና የመካከለኛ ደረጃ (8ኛ ክፍል) ማጠናቀቂያ ስርትፊኬት ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።
የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ደረጃ (6ኛ ክፍል) እና የመካከለኛ ደረጃ (8ኛ ክፍል) ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና በሁለት ዙር ፈተናውን ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ መኾኑንም ተገልጿል።
የመጀመሪያ ዙር ፈተና የመጀመሪያ ደረጃ (6ኛ ክፍል) ከሰኔ 05 እስከ 06/2017 ዓ.ም እና የመካከለኛ ደረጃ (8ኛ ክፍል) ከሰኔ 03 እስከ 04/2017 ዓ.ም ፈተና መስጫ ቀናት እንዲሆን ተወስኗል ተብሏል።
በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት ተቋማት ከራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት ተፈታኝ ተማሪዎችን በአግባቡ በማዘጋጀት፣ በቅድመ ፈተና፤ በፈተና ወቅት እና በድህረ ፈተና መከናወን ያለባቸውን ዝርዝር ተግባራት ከወዲሁ በመለየት እና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ተግባራትን እንዲያከናውኑ አሳስቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን