
ባሕር ዳር:ሚያዝያ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የቻይና ሕዝብ የፖለቲካ ምክክር ጉባኤ ብሔራዊ ኮሚቴ ምክትል ሊቀ መንበር እና የቻይና የኢንዱስትሪና የንግድ ፌዴሬሽን ሊቀመንበር ጋኦ ዩንሎንግ ጋር ተወያይተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የቻይና ሕዝብ የፖለቲካ ምክክር ጉባኤ ብሔራዊ ኮሚቴ ምክትል ሊቀ መንበር እና የቻይና የኢንዱስትሪና የንግድ ፌዴሬሽን ሊቀመንበር ጋኦ ዩንሎንግ እና የልዑክ ቡድናቸው ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደኅና መጡ እላለሁ ብለዋል።
በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል ያለውን የኢንቨስትመንት፣ የኢኮኖሚ ልማት እና የንግድ ትብብርን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከሊቀ መንበሩ ጋር ውይይት አካሂደናል ነው ያሉት።
ጋኦ ዩንሎንግ ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለችውን የልማት እንቅስቃሴ አድንቀዋል፡፡ በተለይም መዲናችን አዲስ አበባ በእጅጉ እንደተለወጠችና ባዩት ስኬታማ ሥራ መደነቃቸውንም ተናግረዋል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ ለቻይናውያን ባለሀብቶች ምቹ መሆኗን እና በሁኔታዎች የማይቀያየር የሁለቱ ሀገራት ስትራቴጂካዊ አጋርነት በኢኮኖሚው መስክም ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተግባብተናል ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!