
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት በተዋረድ ከሚገኙ የምክር ቤት አፈ ጉባዔዎች፣ ምክትል አፈ ጉባዔዎች፣ ቋሚ ኮሚቴዎች እና የዕቅድ ባለሙያዎች ጋር የ2017 በጀት ዓመትን የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸሙን እየገመገመ ነው።
የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬ ውይይቱ በዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም አፈጻጸሙ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ እንደሚያስችል ገልጸዋል።
እጥረቶችን በማረም እና ጥንካሬዎችን በማስቀጠል በጋራ በመወያየት ቀሪ ሥራዎችንም በቀጣይ ለመፈጸም እንደሚያስችል አንስተዋል።
ተወያዮቹ ለግምገማ የሚቀርበውን ሪፖርት ቀድሞ የደረሳቸው መኾኑን ገልጸዋል። በሚነሱ ሀሳቦች እና ጥያቄዎች ላይ በመወያየት ለቀጣይ ሥራዎች አፈጻጸም የጋራ ግንዛቤ እንደሚያዝም አመላክተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!