
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሀገር አቀፍ እና የፌዴራል ባለድርሻ አካላት በአጀንዳ ማሰባሰብ የሚሳተፉበትን መድረክ ለማዘጋጀት እየተሰናዳ መኾኑን አስታውቋል።
ኮሚሽኑም በሀገር አቀፍ እና በፌዴራል ደረጃ በምክክር ሂደቶች እንዲሳተፉ ከለያቸው ባለድርሻ አካላት አጀንዳ ለማሰባሰብ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑንም አመላክተዋል።
በዚህ ሂደት ኮሚሽኑ በሀገር አቀፍ እና በፌዴራል ደረጃ ለሚገኙ የሃይማኖት ተቋማት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ ማኅበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመንግሥት አካላት፣ ጥሪ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
ሆኖም ግን ኮሚሽኑ በሂደቱ ላይ አካታችነትን እና አሳታፊነትን ከማጎልበት አንፃር ከዚህ ቀደም በሂደቱ ላይ እንዲሳተፉ ከለያቸው ባለድርሻ አካላት በተጨማሪ የሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፎን ማረጋገጥ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል፡፡
እነዚህ የሀገር አቀፍ እና የፌዴራል ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ይህ መድረክ ሀገራዊ ፋይዳቸው የጎላ አጀንዳዎችን እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል፡፡
በሂደቱም የሚከተሉት የባለድርሻ አካላት ተሳትፎን እንዲያደርጉ ጥሪ እየተደረገላቸው ነው። ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው እነዚህ አካላት በወኪሎቻቸው አማካኝነት በሂደቱ ይሳተፋሉ፡፡
1. የፌዴራል መንግሥት ሥራ አሥፈጻሚ
2. የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
3. የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት
4. የክልል ርእሳነ መሥተዳደሮች እና የሁለቱ ከተማ አሥተዳደሮች ከንቲባዎች
5. የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
6. የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
7. የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
8. ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች
9. የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት
10. የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን
11. የኢትዮጵያ አሰሪዎች ፌዴሬሽን
12. የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን
13. የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር
14. የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኮንሰርቲየም
15. የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
16. የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን
17. የኢትዮጵያ አረጋውያንና ጡረተኞች ብሔራዊ ማኅበር
18. የሴቶች ጥምረት ለምክክር
19. የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን
20. የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን
21. የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት
22. የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች
23. ማኅበራዊ አንቂዎች እና ተጽዕኖ ፈጣሪዎች
24. የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት
25. የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ
26. የፌዴራል ሲቪል ማኅበራት
27. የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ካውንስል
28. የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር
29. የፌዴራል የሙያ ማኅበራት
30. የቀድሞ የፖሊስ፣ የመከላከያ ሠራዊት
31. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
32. የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም
33. የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን
34. ኮሚሽነሮች (ከተለያዩ ተቋማት)
35. ተፅእኖ ፈጣሪና ታዋቂ ግለሰቦች
36. የፌዴራል የዩኒቨርሲቲ ተቋማት
37. የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የእድሮች ማኅበራት ጥምረት
38. የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ናቸው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን