
አዲስ አበባ: ሚያዝያ 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ሚያዝያ 20/2017 ዓ.ም የሚከናወነውን የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
የገቢ ማሰባሰቢያው “ኑ ጎንደርን እንሞሽር” በሚል መሪ መልዕክት የሚከናወን ነው ተብሏል።
መግለጫውን የሰጡት የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው ጎንደር የቀደመች ከተማ በመኾኗ ቀደምትነቷን ለማስቀጠል እና የተዋበች ለማድረግ ሥራዎች በመከናወን ላይ ናቸው ብለዋል።
የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ለማስቀጠል እና ጎንደርን ወደ ቀድሞ ከፍታዋ ለመመለስ ለጎንደር ተወላጆች እና የታሪኩ ባለቤት መኾን ለሚፈልጉ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን “ኑ ጎንደርን እንሞሽር” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የልማት ጥሪ የቀረበው እንደ አባቶቻችን ለቀጣዩ ትውልድ የሚኮራበት ታሪክ ሠርቶ ለማለፍ እና ሁሉም ጎንደርን ሲያይ የሚደሰትበትን ተግባር ለማከናወን ነው ብለዋል።
የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙ ሚያዚያ 20/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በሸራተን አዲስ ይከናወናል ተብሏል።
ዘጋቢ: ራሔል ደምሰው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
