
ደሴ: ሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በመርሐ ግብሩ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ወገኖች፣ የክርስትና እና የእስልምና ሃይማኖት አባቶች እና ተከታዮች ተገኝተዋል።
የእንኳን አደረሳቸሁ መልዕክት ያስተላለፉት የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ “እኛ ኢትዮጵያውያን ብዙ የምንኮራባቸው፣ እና ማኅበራዊ መስተጋብራችንን የሚያጠናክሩ እሴቶች ያሉን ሲኾን የጋራ ማዕድ መጋራት አንዱ ማሳያችን ነው” ብለዋል።
ከደጋግ ኢትዮጵያውን ከአባት እና እናቶችን የተረከብነውን በጎ ተግባር በበዓላት ወቅት ብቻ ሳይኾን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር የገጠማቸው ወገኖችን በሀሳብ፣ በገንዘብ፣ በጉልበት እና በቻሉት አቅም ሁሉ በተለይም ባለሀብቶች ማገዝ እንዳለባቸው ከንቲባው አሳስበዋል።
አብሮ ከመብላት፣ ከመጠጣት በሻገር በትብብር የመሥራት፣ በጋራ ስለመለወጥ እና በጋራ ስለሀገር እድገት ወደ ማሰብ መሸጋገር እንደሚገባም አቶ ሳሙኤል አመላክተዋል።
በማዕድ ማጋራቱ የተገኙ ወገኖች ለከተማ አሥተዳደሩ ምሥጋና አቅርበው በቀጣይ መንግሥት ለሚያከናውናቸው የልማት እና የሰላም ሥራዎች የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
የማእድ ማጋራቱን የከተማው ባለሀብቶች፣ የክርስትና እና እስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ያዘጋጁት መኾኑ ተገልጿል።
ዘጋቢ : ባለ አለምዬ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን