ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየሠራ መኾኑን የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ገለጸ።

17

ከሚሴ: ሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ)በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ የ2017/18 የምርት ዘመን የሰብል ልማት ንቅናቄ መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሂዷል።

በመድረኩ የተሳተፉ የወረዳ የሥራ ኀላፊዎች በምርት ዘመኑ የተሻለ ምርት ለማምረት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሠሩ መኾኑን ገልጸዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ ምክትል ኀላፊ ሀሰን ሰይድ በ2017/18 የምርት ዘመን ከ58 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በሰብል በመሸፈን ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማምረት ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን ተናግረዋል።

የተያዘው እቅድ እንዲሳካ ከ50 ሺህ ኩንታል በላይ ሰው ሠራሽ የአፈር ማዳበሪያ እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል። ከ300 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ መዘጋጀቱንም አስረድተዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ አሕመድ አሊ በምርት ዘመኑ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከራስ አልፎ ለኢንዱስትሪዎች እና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ መሥራት ይገባል ብለዋል።

የተሻለ ምርት ለማምረት ግብርናውን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ ብሔረሰብ አሥተዳደሩ ትኩረት አድርጎ እንደሚሠራም ገልጸዋል።

ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በፖፕ ፍራንሲስ ሕልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ።
Next articleበአዲስ አበባ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች የከተማዋን ዕድገት የሚያፋጥኑ መኾናቸው ተገለጸ።