
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ፕሬዝደንቱ ለኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብጽዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በላኩት የሀዘን መግለጫ ለቤተሰቦቻቸውና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!