በመልካም አስተሳሰብ እና ተግባር ብቁ የኾኑ መሪዎችን እና አባላትን ለማፍራት ትኩረት መሰጠቱ ተገለጸ።

20

ባሕር ዳር:ሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ)በሰሜን ጎጃም ዞን ጠንካራ ፓርቲ እና መንግሥት በመገንባት ሁለተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈጻጸም በዞን ደረጃ እየተገመገመ ነው።

በዘጠኝ ወሩ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)፣ የርእሰ መሥተዳድሩ የኢኮኖሚ አማካሪ ቀለመወርቅ ምህረቴን ጨምሮ የዞን የሥራ አሥፈፃሚዎች፣ የወረዳ እና የከተማ አስተባባሪዎች ተሳትፈዋል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት በየዘርፉ የተገኙ ለውጦች በጥንካሬ እና በድክመት እየተመዘኑ፣ መልካም ተሞክሮዎች በመለየት በዞን፣ በወረዳ እና ከተማ ደረጃ የብልጽግና ሥራዎች ግባቸውን እንዲመቱ በቀጣይ ወራት የሚከናወኑ ተግባራትን ለማጠናከር የሚያግዝ ውይይት እየተካሄደ ነው።

እስካሁን የተመዘገበው የሥራ ውጤት ሰፊ መኾኑም ተመላክቷል። ይህ ስኬት እንዳያዘናጋ በመልካም አስተሳሰብ እና በተግባር ብቁ የኾኑ መሪዎችን እና አባላትን ለማፍራት የሚሠሩ ሥራዎች ይበልጥ እንዲጎለብቱ ትኩረት ተሰጥቷል።

የዞኑን ፖለቲካዊ ሁኔታ፣ የልማት እና የሕግ ማስከበር ሥራዎችን በመገምገም ለቀጣይ ወራት አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡም ተመላክቷል።

በመድረኩ የዘጠኝ ወራት የፓርቲ፣ የልማት፣ የመንግሥት አሥተዳደር፣ የጸጥታ እና የሕግ ማስከበር ዘርፎች ሪፖርቶች ቀርበዋል።

ከአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በመድረኩ የተደረጉ ውይይቶች በቀጣይ ወራት ለተጠናከረ እና ውጤታማ ሥራ ወሳኝ ግብዓት እንደሚኾኑም ይጠበቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleመጤ እና ወራሪ አረሞች የግብርናው ዘርፍ ፈተና ኾነዋል።
Next articleበጀትን በአግባቡ በመጠቀም ልማትን ለማፋጠን የሁሉንም ርብርብ ይጠይቃል፡፡