ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጠል አስታወቀ።

34

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለም ባንክ ግሩፕ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ዓመታዊ የፀደይ ወቅት ስብሰባ በዋሺንግተን ዲሲ እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ እና የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ እስመለዓለም ምህረቱ ተገኝተዋል። ሁለቱ መሪዎች ከስብሰባው ጎን ለጎን ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ጋር ተወያይተዋል።

የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት ከኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒሰትር አሕመድ ሽዴ እና ከብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ እስመለዓለም ምህረቱ ጋር ውጤታማ ውይይት አካሂደናል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ላይ እየተገበረችው ባለው የሪፎርም ሥራዎች ዙሪያ መወያያታቸውንም ገልጸዋል። በውይይታችን የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ ልማት እና እድገት ያለውን ጠንካራ አጋርነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠናል ነው ያሉት።

የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ለኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መግላጻቸው ይታወሳል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየፈተና ጥሪ
Next articleየመኖሪያ ቤት ኪራይ እና ሕጉ!