
ባሕር ዳር: ሚያዚያ: 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሮም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ በኾኑት በብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ ፍራንሲስ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል።
ፓትሪያርኩ ለመላው የሮማ ካቶሊካዊ መሪዎች እና በመላው ዓለም ላሉ ምእመናን እንዲሁም በኢትዮጵያ ላሉ ካቶሊካውያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም ሃዘናቸውን መግለጻቸውን ከኢኦተቤ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!