
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ሕልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የርእሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሕልፈት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማቸው ገልጸዋል። ሊቀ ጳጳሱ ለሃይማኖት፣ ለሰብአዊነት እና ለዓለም አቀፍ ሰላም ያበረከቱትን ሀዘን እንደሚያስታውሱም አንስተዋል።
ነፍሳቸው በሰላም እንድታርፍም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!