
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ሕልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፖፕ ፍራንሲስ ሕልፈት የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እገልጻለሁ ብለዋል። ነፍሳቸው በሰላም እንድታርፍም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የእርሳቸው መልካም ሥራ እና የአገልግሎት ትሩፋት ትውልዶችን ማነሳሳቱን እንደሚቀጥልም አመላክተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!