
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የትንሣኤ በዓልን በገላን ጉራ ከሚገኙ የካሳንቺስ ልማት ተነሺዎች ጋር አክብረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት የትንሣኤ በዓልን በገላን ጉራ ከሚገኙ የካሳንቺስ ልማት ተነሺዎች ጋር አሳልፈናል ብለዋል።
ጎስቋላ የነበረውን ከተማ እንቀይረው ያልነው ለጋራ ጥቅም፣ ለልጆቻችን ደስታ እና መጻኢውን ዘመን ለማሳመር ብቻ ነው። የተለወጠችና ከልመና የወጣች ሀገር እውን ከማድረግ ውጪ ሌላ ሃሳብ የለንም ነው ያሉት።
ይህ አዲሱ ሰፈራችሁ የምትኖሩበት ነው። ቀድሞ የኖራችሁበት ሰፈራችሁን ሄዳችሁ እንድታዩት እጋብዛለሁ። ቃል በገባነው መሰረት ካሳንቺስ እጅግ ውብ ሆኗል። ልጆቻችን ተስፋ አላቸው ፣ ከእኛ የተሻለ ሕይወት መኖር ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ትንሣኤ ቅርብ ነው። እኛም እናያለን፣ ልጆቻችንም ይወርሳሉ ብለዋል በመልዕክታቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!