በበዓል ጊዜ በጋራ በማሳለፍ የኢትዮጵያን እሴት የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ገለጹ።

99

አዲስ አበባ: ሚያዚያ 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከካሳንቺስ ለልማት ተነስተዉ በገላን ጉራ የሰፈሩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ጎብኝተዋል። ለበዓል ማዕድም አጋርተዋል።

በማዕድ ማጋራቱ መልእክት ያስተላለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በበዓል ጊዜ ወገንን መጎብኘት እና ያለንን ተካፍሎ በጋራ በማሳለፍ መልካም የኢትዮጵያን እሴት የበለጠ ማጠንከር ይገባል ብለዋል።

ነዋሪዎችም ያሉበትን ሁኔታ ስለተጎበኙ እና በማዕድ ማጋራት መርሐ ግብሩ መሳተፍ በመቻላቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ይህ መልካም ዕሴታችን አንድነትን የሚያጠናክር በመኾኑ ሌሎችም ሊማሩበት የሚገባ ተግባርንም ነው ብለዋል።

ዘጋቢ:- በለጠ ታረቀኝ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ።
Next article” የኢትዮጵያ ትንሣኤ ቅርብ ነው፣ እኛም እናያለን፣ ልጆቻችንም ይወርሳሉ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)