
ደብረ ታቦር: ሚያዚያ 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የስቅለት በዓል በደብረ ታቦር ከተማ ደብረ ልዑላን መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን በተለያዩ ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች እየተከበረ ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሲል የተቀበለውን መከራ እና ግርፋት በማሰብ ነው ቀኑ እየታሰበ ያለው።
የአራቱ ጉባዔያት ምስክር መምህረ መምህራን የንታ በጽሐ ዓለሙ ስቅለቱ ትንሣኤ የተገለጠበት፣ የጥል ግድግዳ የፈረሰበት፣ ሰላም የሰፈነበት ነው ብለዋል። “መዕመኑ ልቦናውን ለፍቅር እና ለይቅርታ ክፍት ማድረግ አለበት” ነው ያሉት።
በቤተ ክርስቲያኑ ተገኝተን ያነጋገርናቸው የሃይማኖቱ ተከታዮችም ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለውን መከራ በማሰብ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ አስተምህሮው መሠረት የስቅለትን በዓል እያከበሩ መኾኑን ተናግረዋል።
መጭውን የትንሣኤ በዓልም በመተሳሰብ እና በመረዳዳት እናከብረዋለን ነው ያሉት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን