ዕለተ አርብ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ፍቅሩን የገለጸበት ዕለት ነው።

18

ፍኖተ ሰላም: ሚያዝያ 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በፍኖተ ሰላም ከተማ ፈለገ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል የስቅለት በዓል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች እየተከበረ ነው።

የስቅለት በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳም የገባውን ቃል የፈጸመበት ዕለት ነው።

በዚሁ ዕለት ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሲል የተቀበለውን መከራ እየታሰበ፣ ግብረ ሕማማት እየተነበበ በጸሎት እና በስግደት ቀኑን ሙሉ የሚከወንበት በዓል ነው።

በፍኖተ ሰላም ከተማ ፈለገ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ምዕመናን እና የሃይማኖት አባቶች በተገኙበት ከጠዋት ጀምሮ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች ሥርዓቱ እየተከበረ ይገኛል።

በፍኖተ ሰላም ከተማ ወረዳ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል ኀላፊ መምህር ብሩህ አንላይ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ኾኖ ሳለ ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ በአይሁዶች ተይዞ የተሰቀለበት ዕለት መኾኑን ተናግረዋል።

ዕለተ አርብ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ፍቅሩን የገለጸበት ዕለት በመኾኑ ምዕመናንም ከዚህ ትምህርት በመውሰድ መተባበርን፣ መረዳዳትን እና መተሳሰብን ልንቀስም ይገባል ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እየተከበረ ነው።
Next articleየስቅለት በዓል የበደልናቸውን ብቻ ሳይኾን የበደሉንን ጭምር ይቅር የማለት ምሳሌ መኾኑን መጋቢ ሐዲስ መምህር አሸተ ዜናዊ ተናገሩ።