የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እየተከበረ ነው።

20

አዲስ አበባ: ሚያዝያ 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዕለተ አርብ ኢየሱስ ክርስቶስ 14ቱን ግብረ ሕማማት በግፍ የተቀበለበት ዕለት ነው። በሃይማኖቱ ተከታዮች ዘንድም ቀኑ ልዩ ትርጉም የሚሰጠው ነው።

ከሊዮስጥራ እስከ ቀራኒዮ ድረስ መስቀሉን ተሸክሞ የተጓዘበት፣ የኋሊት በመታሰርም የተገረፈበት፣ የተሰቀለበት፣ አይሁዳውያን የተዘባበቱበት ዕለት ነው።

ለሰው ልጆች ሲል መከራን የተቀበለበት እና ራሱን አሳልፎ የሰጠበት ዕለት መኾኑን የሃይማኖቱ ሊቃውንት ይናገራሉ።

ዛሬ የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሃይማኖተ ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው።

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አዲስ አበባ ከተማ አራት ኪሎ በሚገኘው በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ተገኝቶ የስቅለት በዓል አከባበርን ተመልክቷል።

በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እየተከበረ በሚገኘው የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያሪክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ፣ ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ አባቶች እና ምዕመናን ተገኝተዋል። በዓሉ በስግደት፣ በፆም እና በጸሎት እየተከበረ ይገኛል።

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽንም የበዓሉን ኹነት በቀጥታ ስርጭት ለአድማጭ ተመልካች እያደረሰ ይገኛል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየስቅለት ተዓምራት እና አስተምህሮው!
Next articleዕለተ አርብ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ፍቅሩን የገለጸበት ዕለት ነው።