የትንሳኤ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር ዝግጅት ማጠናቀቁን የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

24

ደባርቅ: ሚያዚያ 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የትንሳኤ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር ዝግጅት ማጠናቀቁን የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፀጥታ ኀይሉ የቁጥጥርና የጥበቃ ሥራ በተጨማሪ ማኅበረሰቡ ንቁ ተሳታፊ ሊሆን እንደሚገባም ጥሪ ቀርቧል።

የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ደሳለኝ አበራ በበዓሉ ከበራ ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉ የወንጀል ተግባራትን ለመከላከል የፀጥታ ኀይሉ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ስምሪት ወስዷል ብለዋል።

በበዓል ወቅት ሊፈፀሙ ከሚችሉ ወንጀሎች መካከል ስርቆት እና የሀሰተኛ ብር ኖት ዝውውር በሰፊው ሊኖር እንደሚችል ገልጸዋል። ኅብረተሰቡም በግብይት ወቅት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

ምዕመናን ከሃይማኖት አባቶችና ከፀጥታ መዋቅሩ የሚሰጡ መመሪያዎችን በቀናነት ተቀብለው በመተግበር የተለመደ መልካም ትብብራቸውን እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።

ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮችም መልካም የትንሳኤ በዓል እንዲሆን መልካም ምኞቻቸውን ገልጸዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዝቅተኛ ገቢ ለሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ አደረገ።
Next articleቃል በተግባር የተፈጸመባት አርብ!