የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዝቅተኛ ገቢ ለሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ አደረገ።

21

ደብረ ማርቆስ: ሚያዝያ 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት በከተማዋ በዝቅተኛ ገቢ ለሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ድጋፍ አድርጓል።

የዲስትሪክቱ ኀላፊ አፈወርቅ ሰንደቁ ባንኩ ማኅበራዊ ኀላፊነቱን ለመወጣት በዝቅተኛ ገቢ ለሚኖሩ 100 ለሚኾኑ ዜጎች የምግብ እና የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አድርጓል ብለዋል።

ባንኩ ከዚህ በፊትም የኢድ አልፈጥርን በዓል ምክንያት በማድረግ ለዜጎች ድጋፍ ማድረጉን የገለጹት ኀላፊው ቀጣይም ማኅበራዊ ኀላፊነቱን ለመወጣት የሚሠራ ተቋም ነው ብለዋል።

ድጋፍ ያገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችም ባንኩ በዓልን በደስታ ማሳለፍ እንዲችሉ ድጋፍ በማድረጉ ምሥጋናቸውን አቅርበዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወልድያ ዲስትሪክት ለአቅመ ደካማ ወገኖች ለበዓል ድጋፍ አደረገ።
Next articleየትንሳኤ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር ዝግጅት ማጠናቀቁን የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።