
ወልድያ:ሚያዝያ 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወልድያ ዲስትሪክት ለ100 አቅመ ደካማ ወገኖች ነው የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ድጋፍ ያደረገው።
የወልድያ ዲስትሪክት ዳይሬክተር ሰኢድ አሊ ባንኩ ከፋይናንስ አገልግሎቱ ባሻገር ማኅበራዊ ግዴታውን የመወጣት ኀላፊነት ስላለበት 300 ሺህ ብር ወጭ በማድረግ ለእያንዳዳቸው አንድ ሺህ 500 ጥሬ ብር፣ ሦስት ሊትር ዘይት እና አምስት ኪሎ ዱቄት ድጋፍ አድርጓል ነው ያሉት።
ባንኩ ዛሬ የደረሰበት ከፍተኛ አቅም ከምስረታው ጀምሮ ከባንኩ ጋር ይሠሩ የነበሩ ወገኖች ዘላቂ አብሮነት ውጤት ነው ያሉት ዳይሬክተሩ እነዚህ ወገኖች በዘመናቸው ለባንኩ ላበረከቱት ድርሻ ምሥጋናም ጭምር ነው ብለዋል።
ባንኩ ለሜቄዶንያ እንዲኹም የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች የድርሻውን አበርክቷል ነው ያሉት።
ወደፊትም ማኅበራዊ ኀላፊነቱን የመወጣት ሂደቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖች በበኩላቸው በዓል ሲደርስ እንዴት እንውል ይኾን የሚል ጭንቀት አድሮብን ነበር፤ ዛሬ ባንኩ የለገሰን የበዓል ስጦታ ጭንቀታችንን ያቀለለ ነውና እናመሠግናለን ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን