
ወልድያ: ሚያዝያ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የክልሉ እና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በሰሜን ወሎ ዞን የሀራ ከተማን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።
የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እንድሪስ አብዱ፣ የአማራ ክልል ኅብረት ሥራ ማኅበራት ማስፋፊያ ባለሥልጣን ምክትል ኀላፊ እንዳልካቸው ሲሳይ፣ የሰሜን ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ከድር ሙስጦፋ፣ የሰሜን ወሎ ዞን ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኀላፊ ሞላ ደሱ እና ሌሎች የክልል የሥራ ኀላፊዎች በሰሜን ወሎ ዞን ሀራ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የኢንቨስትመንት ተግባራትን ጎብኝተዋል።
የክልሉ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እንድሪስ አብዱ በከተማዋ ያለው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ አበረታች መኾኑን ገልጸዋል።
የክልሉ መንግሥት ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ባለሀብቶች ምቹ የኾነ የኢንቨስትመንት ፍስሰትን ለመፍጠር ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው ብለዋል።
ሀራ ለኢንቨስትመንት እምቅ አቅም ያላት ከተማ ናት ያሉት ኀላፊው የኢንቨስትመንት ማዕከል እንድትኾን ለማድረግ ቢሮው አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ነው ያሉት።
የሀራ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሙሐመድ ሰኢድ ከተማ አሥተዳደሩ ለኢንቨስትመንት አስፈላጊ የኾኑ መሠረተ ልማቶችን ለማሟላት በትኩረት እየሠራ እንደኾነም አስረድተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን