የጸሎተ ሐሙስ በዓል በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን እየተከበረ ነው።

37

አዲስ አበባ: ሚያዚያ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጸሎተ ሐሙስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን እየተከበረ ነው።

በሥነ ሥርዓቱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ጨምሮ ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተዋል።

ጸሎተ ሐሙስ ሕጽበተ ሐሙስ፣ የምስጢር ቀን፣ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ፣ የነፃነት ሐሙስ እየተባለ ይጠራል፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ቀንም የሚታሰብበት፣ ተምሳሌተ ተግባሩም የሚፈፀምበት ዕለት ነው።

ሕጽበተ ሐሙስነቱን ለማስታወስ ዛሬም ሊቃነ ጳጳሳት እና ቀሳውስትቱ በምዕመኑ መካከል ተገኝተው በቤተ ክርስቲያን የተገኙ ምእመናንን እግር በወይራ ቅጠል የሚያጥቡበት ዕለት ነው።

ዘጋቢ:- አንዱዓለም መናን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየመገናኛ ብዙሃን አዋጅን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ።
Next articleየአማራ ክልል መንግሥት ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ባለሀብቶች ምቹ የኾነ የኢንቨስትመንት ፍስሰትን ለመፍጠር በትኩረት እየሠራ ነው።