
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸሙን ከተቋሙ የሥራ ኀላፊዎች፣ ከሌሎች ተቋማት ከተጋበዙ እንግዶች እና ከተቋሙ ባለሙያዎች ጋር በመኾን ገምግሟል።
በዕለቱ ንግግር ያደረጉት መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) ባለፉት ዘጠኝ ወራት ቢሮው ዋና ዋና ተግባራት በዕቅዱ መሠረት እንዲተገበር በርትቶ ከመሥራት በተጓዳኝ “የክልሉ ሕዝብ በአንጻራዊነት ሰላማዊ ኑሮ እንዲኖር በርካታ ጥረት ተደርጓል ብለዋል።
የክልሉ ሕዝብ ወደ ቀደሞ ሰላሙ እንዲመለስ የመንግሥት ሠራተኛውም ኾነ የክልሉ ነዋሪ ከተሰጠው ሙያዊ ኀላፊነት በተጨማሪ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ለክልሉ ሰላም በዲጅታል ሚዲያው በኩል በተለይም ሀሰተኛ መረጃዎችን በማክሸፍ ረገድ ሰፊ ሥራ ሠርተናል ያሉት ኀላፊው እነዚህን ሀገር አፍራሽ እና ግጭት ቀስቃሽ የኾኑ መረጃዎችን በዲጂታል ሚዲያ የመመከት ተግባርም ተከናውኗል ነው ያሉት።
በግምገማ መድረኩ የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ምክትል ኀላፊ ሙሉነህ ዘበነ ሁላችንም በተደመረ አቅም ብዙ ጥረቶች አድርገናል ብለዋል።
ኮሙዩኒኬሽን ተቋሙ ውጤታማና ጥሩ ፈጻሚ እንዲኾን ከሌሎች ተቋማት በተሻለ ሪፎርም መደረግ እና መደገፍ እንዳለበትም በአጽንኦት አንስተዋል።
የቢሮው ምክትል ኀላፊ ትብለጥ መንገሻ በዚህ በአስቸጋሪ ሰዓት ጥሩ የአፈጻጸም በመመዝገቡ የተቋሙን ሠራተኞች የሚያስመሰግን ነው ብለዋል።
አሁን ባለው ኹኔታ አንጻራዊ ሰላም በመምጣቱ ከዚህ የተሻለ መፈጸም እንደምንችል ሙሉ እምነት አለኝ ማለታቸውን ከኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘ መረጃ ያሳያል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
