የጤና ተቋማት የሕዝቡን የጤና ችግሮች እንዲፈቱ ሥራዎችን በጋራ መሥራት ያስፈልጋል።

25

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ቢሮ ኀላፊ ሙሉነህ ዘበነ በጤናው ዘርፍ የተመዘገቡ ለውጦች እና ውጤቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸው የሚዲያ አካላት ከፍተኛ ሚና አላቸው ብለዋል።

ኅብረተሰቡን ማዕከል ያደረገ መረጃ በማድረስ ከዚህ ቀደም ከሚሠራበት የሚዲያ ሥራ በተለየ መንገድ በመሥራት የተጀመሩትን የጤናውን ዘርፍ ለውጦች ለማስቀጠል በትጋት መሥራት አለብንም ብለዋል።

በአማራ ክልል ጤና ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ታምራት ማለደ በበኩላቸው የሚዲያ ፎረም አስፈላጊነት በሚዲያ ባለሙያዎች በኩል የሚታዩ አላስፈላጊ እና አወዛጋቢ የጤና እና ጤና ነክ ጉዳዮች እንዲኹም መረጃዎች ላይ ተመሳሳይ እና ወጥ ግንዛቤ በመያዝ ለመሥራት ያስችላል ብለዋል።

የጤና ዘርፉ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ፍትሐዊ ጥራት ያለው ሁሉን አቀፍ የጤና ሥርዓት በመፍጠር ማገልገል እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የክልሉ የጤና ተቋማት የሕዝቡን የጤና ችግሮች ሊፈቱ በሚችል መልኩ ሥራዎችን በጋራ መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በመድረኩም የክልሉ ጤና ቢሮ እና የሚዲያዎች የ2017 ዓመት የ9 ወር የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በክልሉ የሚገኙ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ኀላፊ እና ባለሙያዎች በመድረኩ ተሳታፊዎች ነበሩ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleከ10 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር መጓጓዙን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።
Next articleየአማራ ልማት ማኅበር አቅም ለማሳደግ ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ፡፡