ከ10 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር መጓጓዙን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።

23

ባሕር ዳር:ሚያዝያ 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአፈር ማዳበሪያ የማጓጓዝ ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ለ2017/18 የምርት ዘመን ግብዓት ከ10 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዟል።

ለ2017/18 የምርት ዘመን ግብዓት የሚሆን 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ወይም 24 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ገዝቶ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ ነው።

ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የአፈር ማዳበሪያው የተጓጓዘው በድንበር ተሻጋሪ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ እና በባቡር ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ለአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነሮች ሹመት ሰጡ።
Next articleየጤና ተቋማት የሕዝቡን የጤና ችግሮች እንዲፈቱ ሥራዎችን በጋራ መሥራት ያስፈልጋል።