
ባሕር ዳር:ሚያዝያ 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) “በራስ አቅም የመልማት ምልክት” በሚል መሪ መልዕክት ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።
በጠቅላላ ጉባዔው የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፉዬ፣ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) እና ሌሎችም ከፍተኛ መሪዎች ተገኝተዋል።
አልማ “በራስ አቅም የመልማት ምልክት” በሚል ዋና መልእክቱ ሁሉን አቀፍ በኾኑ የሕዝብ የልማት ሥራዎች ላይ የሚሠራ ማኅበር ነው።
ማኅበሩ በዛሬው 15ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴው እንደሚገመገም ተገልጿል። ለማኅበሩ አሻራቸውን ላበረከቱ ተቋማትም እውቅና እንደሚሰጥ ይጠበቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
