
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በ2025 የፒ4ጂ ቬይትናም ጉባዔ ላይም ይሳተፋሉ።
በቆይታቸው ከቬይትናም የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች በማምረት ወደ ውጭ የሚልከውን ቶዮ ሶላር የተባለውን ፋብሪካ ጎብኝተዋል። ድርጅቱ በቅርቡ በሀዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ በመግባት በኢትዮጵያ ሥራ ጀምሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርጅቱ ከፀሐይ ኃይል ማመንጫ ምርት ባሻገር የኃይል ማመንጫ ፋብሪካ እንዲያቋቁም አበረታተዋል። ይኽም ሀገራችን ከያዘችው የአረንጓዴ አሻራ ፖሊሲ ጋር የተናበበ በማደግ ላይ ላለው የኃይል ጥያቄም ምላሽ በመስጠት ሊያግዝ የሚችል መኾኑን አውስተዋል።
