“ሀገራዊ የብልፅግና ግባችንን እና ዓመታዊ እቅዶቻችንን ለማሳካት ተቋማት ቀን ከሌት ሊተጉ ይገባል” ተመስገን ጥሩነህ

21

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ እና የዘርፎች ዕቅድ አፈጻጸም ከፌደራል ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ጋር መገምገም መጀመሩን ገልጸዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በቆይታችንም በ100 ቀናት የትኩረት ማዕከል የሆኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ የተገኙ ውጤቶችን፣ የታዩ ክፍተቶችን እና የትኩረት አቅጣጫዎች ከተቋማቱ የስራ ኃላፊዎች ጋር በጋራ እናያለን” ብለዋል በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፡፡

ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ እና ሪፎርም ትግበራ በተለያዩ መስኮች በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። የዘርፎች አፈጻጸምም የላቀ ነው፤ እነዚህ ድሎቻችን እንደ መንግሥት የመፈፀም አቅማችንን ማሳያዎች ናቸው ብለዋል፡፡

በቀሪ ወራት መፈፀም ያለባቸውን ተግባራት በመለየት በዓመቱ ለማሳካት የተያዙ ትልሞችን በተሟላ መልኩ ለመፈፀም ሁሉም አካላት በትኩረት መሥራት እንደሚገባውም አስገንዝበዋል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article2 ቢሊዮን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች በአዲስ ፈቃድ መሰጠቱን የምዕራብ ጎንደር ዞን ገለጸ።
Next articleሕዝብ መከላከል በሚችላቸው በሽታዎች እንዳይጠቃ ጠንካራ የተግባቦት ሥራ እንደሚያስፈልግ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ገለጸ።