የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሸለመ።

40

ባሕር ዳር:ሚያዝያ 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጀርመን ሀምቡርግ በተካሄዱ ሁለት መርሐግብሮች ተሸልሟል።

አየር መንገዱ ሽልማቱን ያገኘው “በአፍሪካ ምርጥ የበረራ ላይ ምግብ አቅርቦት አየር መንገድ” ሽልማት እና በአፍሪካ በቀዳሚነት በተረከባቸው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላኖቹ በሚሰጣቸው ዘመናዊ አገልግሎቶች “Cabin Concept of the Year 2025” ነው።

አየር መንገዱ በተሰጠው ሽልማት ደስተኛ መኾኑን ገልጿል። ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው እነዚህ ሽልማቶች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ዓለም አቀፍ እውቅና ያጎናፀፉና በዓለም ደረጃ ያለውን ተወዳዳሪነት የሚያጠናክሩ ናቸው ተብሏል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልእክት:-
Next article2 ቢሊዮን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች በአዲስ ፈቃድ መሰጠቱን የምዕራብ ጎንደር ዞን ገለጸ።