
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል ሲያካሂደው የሰነበተው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የማጠቃለያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
በማጠቃለያ ዝግጅቱ የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች እና በአጀንዳ ማሰባሰቡ ሂደት የተሳተፉ ተወካዮች ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከመጋቢት 27/2017 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ክልል አጀንዳ ሲያሰባስብ መሰንበቱ ይታወሳል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
