
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር በዳንግላ ከተማ በሕገወጥ መንገድ ከላይ ከሰል በመጫን በስር የተፈታ የመንግሥት ተሽከርካሪ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር መዋሉን የከተማ አሥተዳደሩ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
የዳንግላ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ጀጃው ሞላ (ኢ.ር) እንደገለጹት በታጠቁ ኀይሎች አማካኝነት የመንግሥት ተሽከርካሪው ከአፈሳ ወደ በሕርዳር ሲጓዝ ነው በአካባቢው ማኅብረሰብ በተሰጠው ጥቆማ በቁጥጥር ስር የዋለው።
የከተማ አሥተዳደሩ የሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ተወካይ ኀላፊ ብርሃኑ ገድፍ የአካባቢው ማኅበረሰብ እነዚህን እና መሰል ወንጀሎች ሲፈጠሩ ጥቆማ መስጠት እንዳለበት ማሳሰባቸውን የዳንግላ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
