የፈለገ ሕይዎት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለዐይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መኾኑን አስታወቀ።

34

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዐይን ሞራ ግርዶሽ ሕክምና አገልግሎት በመስጠት በኩል በትኩረት እየተሠራ መኾኑን የፈለገ ሕይዎት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታውቋል። የሆስፒታሉ የዐይን ሕክምና ክፍል አሥተባባሪ ድረስ ዓለማየሁ በባሕር ዳር እና አካባቢው ለሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ነጻ የዐይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና ሕክምና እየተሰጠ ነው ብለዋል። የመጀመሪያው ዙር በዛሬው ይጠናቀቃል ነው ያሉት።

በዚህ ዓመት ለ719 ሰዎች በመደበኛ እና ለ1 ሺህ 399 ሰዎች ደግሞ በዘመቻ የዐይን ሞራ ግርዶሽ ሕክምና ተሰጥቷል ብለዋል። አሥተባባሪው እንዳሉት ሆስፒታሉ በቀጣይ “ኪዩር ብላይንድነስ ፕሮጀክት” ከተባለ ድርጅት ጋር በመተባበር ከግንቦት 15 እስከ 19/2017 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ አምስት ቀናት ነጻ የዐይን ሞራ ቀዶ ጥገና ሕክምና እንደሚሰጥም ጠቁመዋል።

በዘመቻው 1 ሺህ ለሚኾኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ነው ያሉት።

በታቀደው መርሐ ግብር መረረትም፦

👉 ከሚያዚያ 25 እስከ 26/2017 ዓ.ም ድረስ በመራዊ እና ዳንግላ ጤና ጣቢያ

👉 ከግንቦት 2 እስከ 3/2017 ዓ.ም ድረስ በሊበን እና ዱርቤቴ ጤና ጣቢያ

👉ከግንቦት 9 እስከ 10/2017 ዓ.ም ድረስ አዴት እና ወረታ ጤና ጣቢያ

👉 ከሚያዚያ 25 እስከ ግንቦት 10/2017 ዓ.ም ድረስ ደግሞ በፈለገ ሕይዎት ሆስፒታል የልየታ ሥራ የሚሠራ ይኾናልም ብለዋል።

የዐይን ሞራ ግርዶሽ በዋናነት በዕድሜ መጨመር ምክንያት የሚከሰት ሲኾን በስኳር በሽታ እና ተያያዥ በሽታዎች ምክንያት ሊከሰት እንደሚችል ነው አሥተባባሪው የገለጹት።

የዐይን ሞራ ግርዶሽ ዕይታን የሚቀንስ እና ዐይነ ስውርነትን የሚያስከትል ቁጥር አንድ ምክንያት ተደርጎ ይወሰዳል ነው ያሉት። ቀዶ ጥገና ደግሞ ዋነኛ መፍትሔው ነው ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleአሚኮ እለታዊ የምንዛሬ መረጃ ሚያዝያ 3/2017 ዓ.ም
Next articleበሕገወጥ መንገድ ወደሌላ አካባቢ ሊዘዋወር የነበረ ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ዋለ።