
ወልድያ: ሚያዝያ 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በተሻሻለው የአደረጃጀት፣ የአሠራር፣ የመመሪያ፣ የኢንስፔክሽን እና ሥነ ምግባር ኮሚሽን መተዳደሪያ ደንብ ላይ ከመምሪያ እስከ ቀበሌ ላሉ የመንግሥት እና የፓርቲ የሥራ ኀላፊዎች ሥልጠና ሰጥቷል።
የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋዬ ገብሬ ሥልጠናው በፓርቲው ውስጥ ያለውን የሰው ኀይል በማደራጀት እና በማብቃት የፖርቲውን ተልዕኮ መፈፀም የሚችሉ አባላት እና መሪዎችን ለማፍራት ትኩረት ያደረገ መኾኑን ገልጸዋል።
ጠንካራ ፓርቲ መፍጠር የፓርቲው ዘላቂ እቅድ መኾኑን አስረድተዋል። ጠንካራ ፓርቲ ለመፍጠር የተሻሉ አባላትን በመመልመል እና በማደራጀት በተከታታይ ግምገማ እና ሥልጠና የማብቃት ሥራ ይሠራል ነው ያሉት።
ሥልጠናውም አባላትን በማብቃት ጠንካራ መሪ የመፍጠር ሂደትን ስኬታማ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
