
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል አጀንዳ የማሠባሠብ ሥራውን እያከናወነ ነው።
የወረዳ ማኅበረሰብ ተወካዮች የአጀንዳ ማሠባሠብ እና ለአጠቃላይ የምክክር ጉባኤው ወኪሎችን የመምረጥ ሥራ መጋቢት 01/2017 ዓ.ም መጠናቀቁ ይታወሳል።
መጋቢት 02/2017 ዓ.ም ደግሞ አምስት ባለድርሻ አካላትን ያካተተው ክልላዊ የምክክር መድረክ ተጀምሯል።
ዛሬ በምክክር ሂደቱ ላይ የተገኙት አምስቱ ባለድርሻ አካላትም፡-
👉የመንግሥት ተቋማት ተወካዮች
👉መንግሥታዊ ያልኾኑ ተቋማት እና ማኅበራት ተወካዮች
👉የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች
👉ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እና
👉 በመጀመሪያው ዙር ምክክር ለሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የተመረጡ የወረዳ ማኅበረሰብ ወኪሎች ናቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
