
ጎንደር: ሚያዝያ 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ በሴፍትኔት መርሐ ግብር በእደ ጥበብ ሥራ ላይ የተሠማሩ ሴቶች ጥጥ በመፍተል፣ ባሕላዊ አልባሳትን በማዘጋጀት እና ስፌት በመሥፋት ተጠቃሚ መኾናቸውን እትጌ ሙሉጌታ ተናግረዋል።
የእደ ጥበብ ሥራው የገቢ ምንጭ በመኾን ሕይዎታቸውን እየለወጠ መኾኑን ያነሱት ደግሞ ወይዘሮ ሰላም ሽመልስ ናቸው።
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ምግብ ዋስትና እና ሴፍትኔት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሀድያ መሐመድ በዘርፉ ከ300 በላይ ሴቶች ተጠቃሚ መኾናቸውን ገልጸዋል።
ሴቶቹ በዓመት ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ በመቆጠብ ተጠቃሚነታቸውን ማሳደግ እንደቻሉም ነው ያብራሩት።
ዘጋቢ – ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
