
የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት ቤንጃሚን ቦል ሜል ከወንድሜ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ይዘውት የመጡትን መልእክት ተቀብያለሁ።
ከምክትል ፕሬዝዳንቱ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገናል። በደቡብ ሱዳን ወቅታዊውን የጸጥታ እና የፖለቲካ ችግሮች ለመፍታት ሁሉን አቀፍ ቀጣናዊ አካሄድ እንደሚያስፈልግ አጽንዖት ሰጥቻለሁ።
ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ሕዝቦች ያላትን የድጋፍ ቁርጠኝነት አጠናክራ ትቀጥላለች።