በአማራ ክልል አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት እንደቀጠለ ነው።

32

ባሕር ዳር: መጋቢት 29/2017 (አሚኮ) ኢትዮጵያውያን የትናንት ችግሮችን ለመፍታት፣ የዛሬ አለመግባባቶችን ለማረም፣ ለነገ ጠባሳ የሚኾኑትን ጥሎ ለማለፍ እየመከሩ ነው።

በምክክር የኢትዮጵያ ችግሮች ይፈታሉ፤ ግጭቶች ይቆማሉ፤ አለመተማመን እና መጠራጠሮች በመተማመን ይቀየራሉና። በታሪክ የተመካከሩ ችግሮቻቸውን ያለ ደም መፋሰስ ፈትተዋል። የሀገራቸውንም ሰላም አጽንተው ዕድገታቸውን አጠናክረዋል።

ኢትዮጵያውያንም ሰላምን አጽንተው፣ አንድነትን አበርትተው ይኖሩ ዘንድ እየመከሩ ነው። ኢትዮጵያ ልጆቿን ሰብስባ እየመከረች ነው። በምክክር ዛሬ ትደምቃለች። ነገም ያለ ቂም እና በቀል ትዋባላችና።

መጋቢት 27 2017 ዓ.ም የጀመረው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ቀጥሏል።

ተሳታፊዎቹ ለሀገር እና ለሕዝብ ይጠይቅማል ባሏቸው አጀንዳዎች ላይ እየተወያዩ ነው። ውይይቱም ለኢትዮጵያ ችግሮች ፍቱን መድኃኒት እንደኾነ ነው የተናገሩት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየፌዴራል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ኮምቦልቻ ከተማ ገቡ።
Next articleየበርሚል ጊዮርጊስ ጸበልን ሀገረ ስብከቱ መከፈቱን እስኪያውጅ ድረስ አማኞች ወደ ቦታው እንዳይሄዱ የምዕራብ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት አሳሰበ፡፡