
ደሴ: መጋቢት 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል፣ የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ.ር) እና ሌሎች የፌዴራል የሥራ ኀላፊዎች ኮምቦልቻ ከተማ ገብተዋል።
የሥራ ኀላፊዎቹ ኮምቦልቻ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የግብርና ሚኒስቴር ድኤታ መለስ መኮንን (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አሥተባባሪ እና የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) እና ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎቹ የቀበሌ ግብርና ባለሙያዎችን የደረጃ ማሻሻያ ፕሮግራም ያስጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ:- ተመስገን አሰፋ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን