የፌደራል መሪዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና የእግር ኳስ ጨዋታ አካሄዱ።

48

ባሕር ዳር: መጋቢት 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ልህቀት በሰው ተኮር አገልግሎት” በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ ማለዳ ሥልጠና እየወሰዱ የሚገኙ የፌዴራል ከፍተኛ መሪዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና የእግር ኳስ ጨዋታ አካሂደዋል።

ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለአካላዊ ጥንካሬ፣ ለአዕምሯዊ ንቃት እና ለጤንነት ያለው ጉልህ ፋይዳ በመገንዘብ ነው መሪዎቹ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ያደረጉት።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደዚህ ዓይነት እንቅስቃሴዎች በመሪዎች መካከል ያለውን ግንኙነት በማጠናከር የተሻለ አንድነትን እንደሚፈጥሩ ገልጸዋል።

ይህ ተግባር የስፖርትን ጠቀሜታ በማጉላት እና በመሪ ደረጃም የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባሕል በማሳደግ ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ነው የተናገሩት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአቶ አደም ፋራህ መልዕክት፦
Next articleሳምንቱ በታሪክ