
ባሕር ዳር: መጋቢት 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራን ጀምሯል።
በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ኢትዮጵያን ሊያድናት የሚችል ምክክር ብቻ ነው ብላችሁ አምናችሁ በመምጣታችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።
ምክክር የአንድ ወገን ሃሳብ ብልጫ የሚወሰድበት ሳይኾን ሁሉም ያለ አንዳች ፍርሃት እና ሀፍረት ሃሳቡን የሚገልጽበት መኾኑን ነው የተናገሩት። ለአማራ ሕዝብ እና ለመላው ኢትዮጵያ የሚበጀውን ሃሳባቸውን በነጻነት እንዲገልጹም አሳስበዋል።
ለምክክር አዲስ አለመኾናቸውንም ተናግረዋል። በምክክር ጊዜ መደማመጥ አስፈላጊ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ መደማመጥ ከሌለ ምክክር የለም ብለዋል። “በምክክር ጊዜ አሸናፊ እና ተሸናፊ የለም፤ ሁሉም አሸናፊ ነው” ለመግባባት ተመካከሩ ነው ያሉት።
በምክክር ሁላችንም አሸናፊዎች በመኾን አንድ ዓይነት ውጤት እናመጣለን ብለዋል። ይችን ሀገር ወደፊት ለማሻገር የሚረዱትን ሃሳቦች እንድትሰጡ አደራ እላችኋለሁ ነው ያሉት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን