“ዛሬ በባሕር ዳር ታሪክ እየተሠራ ነው” ኮሚሽነር አምባሳደር መሐመድ ድሪር

67

ባሕር ዳር: መጋቢት 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራውን ጀምሯል።

በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር መሐመድ ድሪር ታሪክ ለመሥራት የመጣችሁ የአማራ ሕዝብ ተወካዮች ኾይ ደስታዬን እገልጽላችኋለሁ ብለዋል።

“ዛሬ በባሕር ዳር ታሪክ እየተሠራ ነው” ያሉት ኮሚሽነሩ ታሪክ እየተሠራ ነው ስንል የኢትዮጵያ ሕዝብ አብሮን እንደሚሠራ አምነን እየሠራን ነው፤ የተሰማራንበት ሥራ ፍሬውን እያየን ነውም ብለዋል። እኛ በእናንተ መካከል ኾነን ኢትዮጵያ ልጆቿ እርስ በእርስ እየተገዳደሉ እንኖራለን የሚል እምነት የለንም ነው ያሉት።

ለዚህች ሀገር መሠረት በኾነ ሕዝብ መካከል ስንገናኝ ደስ ይለናል ብለዋል። ችግሮችን በምክክር እንፈታለን ብላችሁ የጀግና ውሳኔ ወስናችሁ የአማራ ሕዝብን ወክላችሁ ስለተገኛችሁ ክብር ይገባችኋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ችግር በሀገራዊ ምክክር ይፈታል ብላችሁ ስላመናችሁ እናመሰግናችኋለን ብለዋል። እርስ በእርስ በግጭት ውስጥ ያሉ ወንድማማቾች ወደ ሰላም ተመልሱ እንላችኋለን፣ አባቶች እና እናቶች ይጠሯችኋል ኑ እንመካከር ብለዋል በመልዕክታቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“ሀገር የምትለማው በምክክር ነው ብላችሁ ስለመጣችሁ እናመሰግናችኋለን” ዮናስ አዳዬ (ዶ.ር)
Next article“ዛሬ ለአማራ ሕዝብ ትልቅ ምዕራፍ ነው” ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረሥላሴ