
ባሕር ዳር: መጋቢት 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራውን ጀምሯል።
በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ.ር) ኢትዮጵያ የአፍሪካ ፈርጥ መኾኗ በዓድዋ ተገልጿል ብለዋል።
ያ ዓድዋ ላይ የተገኘው ድል አንድ ላይ መጥተን፣ አንድነታችን ስላጠናከርን ነው ያሉት ኮሚሽነሩ በዓድዋ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይኾን ለመላው ጥቁር ሕዝብ ተምሳሌት ኾነናል ነው ያሉት።
ፊደል ባስተማረ ሕዝብ መካከል ግጭት ሲፈጠር ያሳዝናል ብለዋል። “ሀገር የምትለማው በምክክር ነው ብላችሁ ሁሉንም አልፋችሁ ስለመጣችሁ እናመሰግናችኋለን” ነው ያሉት።
አንድ ላይ ተባብረን የዓባይ ግድብን መሥራት ችለናል፤ ያ ኅብረታችን በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንም መደገም አለበት ብለዋል።
በሀገራዊ ምክክሩ ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር፣ በሕዝብ እና በመንግሥት መካከል እምነት ለመፍጠር ያለመ ነው ብለዋል። ባኮረፍን ቁጥር ወደ ግጭት ሳይኾን ወደ ምክክር እንድንመጣ ባሕል ለማድረግም እንደኮነ ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን